የኳታር ተመክሮ - በኢስላሚክ ባንክ ዊንዶው
================================
እስከ 2011 ዓም በኳታር የኢስላሚክ ባንክ አገልግሎት በመደበኛ ባንኮች ዊንዶው ይሰጥ ነበር። በዚሁ አመት መጨረሻ ተቆጣጣሪው ማዕከላዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሰረት መደበኛ ባንኮቹ እስላማዊ ዊንዶዋቸውን እንዲዘጉ አድርጓል ። ባንኮቹ ከሁለቱ አንዱን እንዲመርጡ አስገድዷል ። መረጃዎች እነደደሚያሳዩት በአሁኑ ጊዜ በኳታር ኢስላሚክ ባንኮቹ እስከ 25% የሚደርስ የገበያ ድርሻ አላቸው።
የኳታር ማዕከላዊ ባንክ ይህን መመሪያ ማውጣት ያስፈለገበትን ምክንያት ሲዘረዝር….
1️⃣ የፈንድ መቀላቀልን ለመግታት
በኢስላሚክ ዊንዶ የሚሰበሰቡ የመደበኛ ባንኮቹ ተቀማጮች ወለድ ነክ ለሆነ ብድር አለመዋላቸውን ማረገኀጥ ስለሚያዳግት
2️⃣ Strengthen Shariah Compliance
ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ ባንኮች ጠንካራ የሸሪዓ ቦርድ ሲኖራቸው ፧ የመደበኛ ባንኮቹ ከተፅዕኖ ነፃ የመሆን እድላቸው መጥበቡ።
3️⃣ Regulatory Clarity & Supervision
ለኢስላሚክ ባንኮች ዩኒፎርም የቁጥጥር ማዕቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፣ ግልጽነት እና አደጋን የመቆጣጠር አሰራር ለማስፈን።
4️⃣ Level Playing Field
መደበኛ ባንኮቹ unfair advantage ያገኛለኡ ብለው ኢስላሚክ ባንኮቹ ቅሬታ ስላቀረቡ እና ተቆጣጣሪው አካልም ታማኝነት እና ፍትሃዊ ተወዳዳሪነትን ማስፈን አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘው።
5️⃣ ጠንካራ እስላማዊ ባንክ እንዲፈጠር ለማስቻል።
====================================
ወደ ሃገራችን ስንመጣ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ተከስተዋል። እንደ አብነት የፈንድ መቀላቀልን ብናይ። CBE Noor እና አምስቱ ባንኮች ከወለድ አልባ መስኮት በዚህ አመት ብቻ የሰበሰቡት 190 ቢሊየን ብር ነው። በወለድ አልባ መልክ ያበደሩት ግን 57.8 ቢሊየን ነው። በመሃሉ ያለውን ከ100 ቢሊየን በላይ…. የማበደር ጣርያቸው ላይ ደርሰው የተሰቃዩት እነዚህ ባንኮች በወለድ አላበደሩትም ቢባል ማን ያምናል?
ማጠቃለያ
=============
ያለ ተቆጣጣሪው አካል ጣልቃ ገብነት ጠንካራ እስላማዊ ባንክ ከቶ ሊፈጠር አይችልም። በሁለት ቢላዋ ከሚበሉት መደበኛ ባንኮች ጋር መወዳደር የማይታሰብ ነው። እንደውም በቅርብ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የሸሪዐ ባንኮችን ሊያጠፍዋቸው ይችላሉ።
ለተቆጣጣሪው አካል አድርሱልኝ።
https://t.me/Aminu_Nuru
ከኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጭ የተገነዘብኩት
================================
ኢትዮ ቴሌኮም 100 ሚሊየን ሼር በመሸጥ 30 ቢሊየን ለማግኘት አስቦ 3.2 ቢሊየን ብር ሰብስቧል። ሽያጩን ለ121 ቀን ቢያራዝመውም ካሰበው 10.7% ገደማ ብቻ ነው የሸጠው።
በነገራችን ላይ በፕሮፔክተሱ ላይ በግልፅ በተጠቀሰው መሰረት የሼሩ “ፓር” ዋጋ 100 ብር ነው። ይህ ማለት ከአጠቃላይ ሽያጩ 3.2ቢሊየኑ ወደ 1 ቢሊየኑ የባለ አክሲየኖች ድርሻ ተብሎ ሲያዝ 2 ቢሊየኑን ቴሌ እንደ ገቢ ይይዘዋል ማለት ነው።
ለምሳሌ አንድ ሰው ዝቅተኛውን 33 ሼር በ 9,900 ብር ሲገዛ የሚሰጠው የድርሻ ሰርተፍኬት የ 3,300 ብር የሚል ነው። ትርፍም የሚሰላለት በዛው ነው። 6,600 ብሩ “ትርፋማውን” የቴሌ ሼር ለማግኘት ያወጣው ወጪ ነው።
አሁን ባለው ሁኔታ ከ400ቢሊየን የተፈቀደ ካፒታሉ 100ቢሊየኑን ቴሌ በአይነት እና በብር የያዘ ሲሆን 1 ቢሊየኑን ሼር ሆልደሮች ይይዙታል ማለት ነው። እስከ 10% የታሰበው ድርሻቸው 1% ይሆናል ማለት ነው።
እንደ እኔ ግንዛቤ ኢትዮ ቴሌኮም በትራንዛክሽኑ በጣም ተጠቃሚ ነው። የሚያጋራው የትርፉን 1% ነው። 2 ቢሊየን ብር እንደ ገቢ ወይንም ካፒታል ማሳደጊያ በሂደቱ ገቢ አድርጓል።
እንደ አጠቃላይ
ከካፒታል ገበያው አላማዎች አንዱ ትናንሽ ብር ያላቸው ሰዎችን ወደ ኢንቨስትመንት መሳብ እና የብር እጥረት ያለባቸው ፕሮጀክቶችን ማስቻል ነው። በዚህ አንፃር ካየነው 47,377 ሰዎች ኢንቨስት ማድረጋቸው እንደ አጠቃላይ የካፒታል ገበያው ተስፋ እንዳለው ያመላክታል። በአንፃሩም እንደ መጀመሪያ ልምድ ቶሎ ትርፍ ጠብቀው የገዙ ካሉና እና ያሰቡት ባይሆን ሌላ ሼር የመግዛት ተነሳሽነታቸው ላይ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል።
ከጥቂት አመታት በፊት የአለማችን ግዙፍ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚዎቹ የነበሩት የአሜሪካ እና የአውሮፖ ባንኮች ነበሩ።
የቻይናን የኢኮኖሚ እድገት ተከትሎ ባንኮችዋ በፋይናንስ ሴክተሩ መሪነቱን ተቆናጠዋል። ይህ የ2023 መረጃ እንደሚያሳየው Top 5 ውስጥ ከገቡት ባንኮች አራቱ የቻይና ባንኮች ናቸው። አመታዊ የእድገት መጠናቸው ደሞ አስገራሚ ነው። የአሜሪካው JPMorgan እንደምንም አምስተኛ ላይ ታይቷል። ሌሎቹ አንጋፋዎቹ የአውሮፓ ባንኮች እስከ 10ኛ ባለው ደረጃ ላይ ይታያሉ።
ቻይና ሴክተር በሴክተር የኢኮኖሚ የበላይነትን ከምእራባዊያን እየነጠቀች ይመስላል።
ከአመታት በፊት ኢህአዲግ የቻይናን የልማታዊ መንግስት ሞዴል መከተል እንፈልጋለን ሲል ሙድ የያዝኩት ላይ መፀፀት ሳይኖርብኝ አይቀርም።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የዋጋ ጭማሪ ብዙዎችን እንዳማረረ እና በIMF ምክርም ደረጃ በደረጃ ጭማሪ እንደሚያደርግ ሰምተናል።
ጄኔሬተር በተፈጥሮ ውሃ እያሽከረከረ እየሸጠ እንዴት አያዋጣውም?? በሚል መንፈስ ተነሳስቼ ፌደራሉ ዋና ኦዲተር መርምሬዋለሁ ብሎ ድርጅቱ በይፋዊ ድረ ገፁ ላይ የለጠፈውን የ2023 ሂሳብ መግለጫ አየሁት።
እንደ እኔ አይታ የታሪፍ ጭማሪ ድርጅቱን የሚታደገው አይደለም
እንደ በ2023 ሂሳብ መግለጫው
••••••••••••••••••••••••••••••
- ገቢው ከ19.09 ቢሊየን ወደ 22.4 ቢሊየን ብር ማለትም በ17.8 % አድጓል።
- በአመቱ ኦፐሬሽናል ፕሮፊቱ 7.3 ቢሊየን ቢሆንም ..: 24 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ኪሳራ አስመዝግቧል። ለዚህ ትልቁን አስተዋፃ ያደረገው ለእርጅና ቅናሽ የተያዘው 8.1 ቢሊየን እና ለብድር አገልግሎት የከፈለው 24 ቢሊየን ብር ነው።
- አጠቃላይ እዳው 324.7 ቢሊየን ብር ደርሷል።
- የኪሳራ ክምችቱ 176.9 ቢሊየን ደርሷል።
ከሂሳብ መግለጫው ላይ ያነበብኳቸው ስጋቶች
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
- የብድር ጫና፧ በአሁኑ ጊዜ ያለበትን የብድር ጫና በምንም አይነት የታሪፍ ማሻሻያ ለማስተካከል የሚታሰብ አይደለም።
- አጠቀኣላይ ያልሰበሰብኩት ብሎ 24 ቢሊየን ብር አሳይቷል ከዚህ ውስጥ 10 ቢሊየኑ ከደንበኞች ያልተሰበሰበ ነው። ከማን እንደሆነ ፈጣሪ ይወቀው።
- የካሽ ሪዘርቩ ማሽቆልቆሉ ለሊኪዩዲቲ አደጋ ያጋልጠዋል።
- በውጭ ምንዛሪ የተበደረው ከፍተኛ ብድር ይዞት የመጣው “Currency Risk”
ከታሪፍ ማሻሻያው በፊት እነዚህ ነጥቦች በአፅንኦት ቢታዩ መልካም ነበር። ያለበለዚያ በታሪፍ ማሻሸያ የሚገኘውን መልሶ ይበላዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
- ብድሩን በሆነ መልኩ “ሪስትራክቸር” ማድረግ። የወለድ ፋታ ማግኘት። 24 ቢሊየን ለብድር አገልግሎት በአመት እጅግ ብዙ ነው። ናላውን ያዞረው ወለድ ነው።
- ኦፐሬሽናል “ኢፊሸንሲ” መጨመር። የተጋነኑ ወጪዎችን መመርመር
- ያልተሰበሰበ የአገልግሎት ዋጋ ብሎ የያዘውን መመርመር። የአሰባሰብ ዘዴ መዘርጋት
- ከፍተኛ ወጪ የሚታይበት የግዥ እና ጥገና ስርአቱን ሂደት መመርመር።
- የኪሳራውን ጫና ለመቀነስ ከፍተኛ Depreciation የተመዘገበባቸውን ንብረቶች አገልግሎት ላይ ካልዋሉ መሸጥ
- ጠንካራ credit policy መዘርጋት። ተገኘ ብሎ ሁሉንም ብድር አለማግበስበስ።
ችግሩ በጥልቀት ሳይመረምሩ ታሪፍ ማሻሻያውን ብቻ ማድረግ ተጠቃሚው ላይ ጫና ይፈጥር ይሆናል እንጂ ድርጅቱን አይታደገውም። ሲስተሙ “ኢፊሸንት” ስላልሆነ ከላይ የተጨመረው ቀጥታ ወደ ትርፍ አይወርድም።
Advertising Scam in Ethiopian Real Estate
መቼም አንድ ሴክተር በጣም የጮኸ ማስታወቂያ ሲበዛበት በግርድፉ ስናየው አቅርቦት እና ፍላጎት ባለ መመጣጠኑ ነው ብለን እናስብ ይሆናል። የኢትዮጵያ ሪል እስቴቱ ማስታወቂያ ብዛት ግን የጤና አይደለም።
Advertising scam ወይም የማስታወቂያ ማጭበርበሪያ ገዠዎችን የተሳሳተ ወይንም ያልተሟላ መረጃ በመስጠት ያልተገባ ጥቅም ለማጋበስ የሚደረግ ጥረት ነው።
በኢትዮጵያው ሪል እስቴት ማስታወቂያ በኔ ግንዛቤ እንደ Advertising scam ያየሁዋቸው ነጥቦች ጥቂቶቹ…..
✅ “ቤቱን እየኖሩበት ይክፈሉ”
ስዕሉን እያሳዩ ቤቱን እየኖሩበት ይክፈሉ ይላል።
✅ Unethical ኢንፍሉየንሰሮችን መጠቀም
ከዚህም ከዚያም በሚወጡት መረጃዎች እንደሰማነው የ10 -15 ሚሊየን ቤት ከአእገሌ ሪል ስቴት ገዛን የሚሉ ዩቱበሮች ለማስታወቂያ ተከፍሏቸው እንደሆነ ነው።
✅ ታዋቂ ግለሰቦች እና የሃይማኖት ሰዎችን ከፊት አድርጎ መጠቀም።
አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት ፎቶዋቸውን ከፊት አድርገው የሸጡባቸው ታዋቂ ሰዎች ችግሩ ሲፈጠር መከራቸውን ሲበሉ አይተናል። ኡስታዞቸኡ ጥሩ ምሳሌ ናቸው ። ሻጮቹ ከሀገር የጠፉም አሉ
✅ ቅድመ ክፍያን እንደ ሙሉ ዋጋ ማስተዋወቅ
“በ890ሺ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ” አስር ፐርሰንቱን ተሙዋሙቶ የከፈለ ሰው ቀሪውን 8 እና 9 ሚሊየን በሁለት አመት ውስጥ ከየት አምጥቶ ነው የሚከፍለው?
✅ “60, 70 80% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው…”
አሁን ባለው ሁኔታ ለኮንስትራክሽን ሴክተር የሚያበድር ባንክ ማግኘት የማይታሰብ ነው። ላልተጀመረ ቤትማ የማይሞከር ነው።
✅ “ ቤትዎን በ18 ወር ወይም 24 ወር እናስረክባለን”
በተጨባጭ እንዳየንው ከሪል እስቴት በአመታት መረከብ የማይታሰብ ነው። የደረሰበት ያውቀዋል።
✅ “የግል ካርታ የተዘጋጀለት”
ይህ የማይታሰብ ነው። ክፍያውን ጨርሰው እየኖሩበት እንኳ ካርታውን ማግኘት ያልቻሉ እልፍ ናቸው። ቀድመው በህንፃው ስለሚበደሩበት የግል ካርታ ማግኘት ህልም ነው።
Disclaimer
በጣት የሚቆጠሩ ትክክለኛ አልሚዎች እና እውነተኛ ማስታወቂያዎች አሉ። ይህ መልዕክት የትኛውም ሪል እስቴት ላይ በተለየ ያነጣጠረ አይደለም።
Bottom line
በማስታወቂያ አትማልሉ። ለመግዛት ስታስቡ ወሉን መርምሩ፣ የሰዎችን ልምድ ጠይቁ፧ ውሉን በባለሞያ አስመርምሩ፧ ባለሞያ አማክሩ። 🫡🫡
https://t.me/Aminu_Nuru